ትምህርተ ሃይማኖት፣ነገረ-ማርያም፣ነገረ-ቅዱሳን፣ኪነጥበብና ስብከቶች የሚቀርብበት ገጽ ነው፡፡
እሑድ 13 ሴፕቴምበር 2015
የኮ/ደ/ብ/ቅ/ሥላሴ ቤ/ክ አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ሃይለ ማርያም መንገሻ የአውደ ዓመት መልካም ምኞትና መልዕ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
አዲሱ አመት የሰላም፣የፍቅር፣ የዕውቀት፣ የልማት፣ የእድገት ፣የትምርህት፣
የስራ፣ የብልጽግና፣የጤና ዘመን እንዲያደርግልን እግዚአብሔር እየተመኘሁ፡፡
የአባቶቻችን የቀናች ሃይማኖት
ቅድመ
አለም ከነበረው ዓለምን ከፈጠረው እግዚአብሔር አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ከሦስት አካል አንዱ እግዚአብሔር ወልድ ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በተለየ አካሉ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ተወለደ፡፡
ይህ ቅድመ
አለም የነበረው ከድንግል ማርያም የተወለደው እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህርይ አንድ
ባህርይ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነው ብሎ በምስጢረ ተዋህዶ ማመን ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ እምነት ነው፡፡
ቀዳማዊ
ደሐራዊ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባህርይ አባቱ ከአብ ከባህርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ አለም ሳይፈጠር የነበረ ሲሆን
ያለ እርሱም ምንም ምን አልተፈጠረም እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ዩሐ.፩፣ ፩-፲
ቃለ እግዚአብሔር
ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ያለዘርዐ ብእሲ ሲወለድ የቅድስት ድንግል ማርያም ማህተመ ድንግልና አልተለወጠም እመቤታችን ድንግል
ማርያም ድንግል ወእም ድንግል ሳለች እናት እናት ሳለች ድንግል ናት፡፡
ስለ ምስጢረ
ድህነት ትምህርት ሲነገር የምስጢረ ድህነት መነሻዋ ድንግል ማርያም ናት ይኸውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ያዳነው ከድንግል
ማርያም በነሳው ሥጋ የሰው ዘርን በመውደዱ እስከ ሞት ድረስ ባደረገው ካሳ ነው፡፡
ቅዱሳን
አበው ሐዋርያት ያስተማሩት የቤተክርስትያን ትምህርት ከሁሉ በላይ የሆነ ሊከለስ ሊለወጥ የማይችል አማናዊ ቃለ እግዚአብሔር ኦርቶዶክሳዊ
እምነት ይህ ነው፡፡
ይህ ኦርቶዶክሳዊ
እምነት ከራሱ ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ከአለም መካከል እስከ አለም ዳርቻ የተሰበከ በሐዋርያት
አበው በሦስት መቶ አስራ ስምንቱ አበው የጸና ኦርቶዶክሳዊ እምነት ነው፡፡
የአባቶቻችን
ሐይማኖት የቀናች ናት ርትዕት ሃይማኖቶሙ ለቅዱሳን አበዊነ ተብሎ እንደ ተነገረው “ኢታንትጉ ወኢትወሰኩ እምዘ መሐርናክሙ ” እኛ
ካስተማርናችሁ እምነት ሌላ አትጨምሩ አትቀንሱ መልአክ እንኳ ከሰማይ መጥቶ ቢያስተምራችሁ አትቀበሉ ተብሎ ተጽፏል፡፡
ሕገ ሃይማኖት
እንደ ስጋዊ ሥርዓት ተለዋዋጭ አይደለም፡፡ሥጋዊ ሥርዓት ከሰው የተገኘ ስለሆነ እንደ ሰዎች ሥልጣኔ ሊያድግ ይችላል ሕገ ሃይማኖት
ግን የተገኘ ከእግዚአብሔር ስለሆነ የእግዚአብሔር ቃል ከሁሉ በላይ ከማንኛውም የተራቀቀና የመጠቀ ስልጣኔ በላይ ስለሆነ ሕገ እግዚአብሔር
አይለወጥም፡፡ በሕገ ሃይማኖት የጸኑ በትሩፋት የጎለመሱ ኦርቶዶክሳውያን ካህናትና ምእመናን በረድኤተ እግዚአብሔር ተጠብቀው በህጉ
ከብረው በጸጋው ተጎብኝተው ይኖራሉ፡፡
ረቡዕ 12 ኦገስት 2015
ከጽንሰታ እስከ ፍልሰታ
እመቤታችን የቅድስት ድንግል ማሪያም ቅድመ አያቶቿ ቴክታና በጥርቃ ይባላሉ፡፡ይህ
ቀራቸው የማይባል ባለጠጎች ነበሩ ምንም ሀብታቸው ቢበዛም የሚያወርሱት
ልጅ ስለሌላቸው ያዝኑ ይተክዙ ነበር፡፡ እግዚአብሔርን ያምኑ ስለነበሩ በራዕይ ነጭ እንቦሳ ከበረታቸው ስትወጣ እንቦሳይቱ እንቦሳ
እየወለደች እስከ ስድስት ስትደርስ ስድስተኛይቱ ጨረቃን ጨረቃይቱ ፀሐይን ስትወልድ አይተዋል፡፡ ሕልም ፈቺ ነበርና ነግረው ደግ
ልጅ ትወልዳላችሁ ጨረቃይቱ ከፍጡራን ሁሉ የምትሆን ናት የፀሐይ ነገር
ግን ንጉስ ይሁን ነቢይ እንጃ አልተገለጸልኝም ብሏቸዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ቴክታ ጸነሰች ሴት ልጅም ወለደች ስሟንም ሂኤሜን አለቻት፡፡
ሄኤሜን ማለት ልመናዬን አገኘሁ ምኞቴን አገኘሁ ማለት ነው፡፡ሄኤሜን ዴርዴንን፡ዴርዴን ቶናን ፡ቶና ሲካርን ፡ ሲካር ሄርሜላን ፡ሄርሜላ
ሐናን ወለደች፡፡ ሐና ማለት በሃይማኖት በምግባር የጸናች በንጽህና በቅድስና የተሸለመች ደግ ፍጥረት ማለት ነው፡፡
ሃና አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ ይሁዳ ለተወለደ ኢያቄም ለሚባል ደግ
ሰው አጋቧት፡፡ በበጎ ሥራ የተራበ እያበሉ የተጠማ እያጠጡ ካላቸው ንብረት ለነዳያን እየመጸወቱ እግዚአብሄርን ዘወትር በጾም በጸሎት
በንጽሕናና በቅድስና እያገለገሉ ይኖሩ ነበር ነገር ግን ልጅ ስላልነበራቸው ያዝኑ ይተክዙ ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ከዛፍ ስር
ተቀምጠው ሳለ ርግብ ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ ዕጽዋቱ አብበው አፍርተው አዩ እነርሱ ግን ልጅ ማጣታቸው የዘወትር ሃዘናቸው ነበርና
እግዚአብሔርን ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ወንድ ቢሆን ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ሴት ብትሆን ለቤተ
እግዚአብሔር መሶበ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ሰፍታ ትኑር ፡፡ እንጨት ሰብራ ውሃ ቀድታ ትርዳን አንልም ብለው ብጽአት ገብተዋል፡፡
ሐምሌ 30 ቀን ሐና ለኢያቄም ግምጃ ሲያስታጥቁህ መቋሚያህ አፍርታ ፍጥረት
ሁሉ ሲመገባት አየሁ አለችው፡፡ ኢያቄምም ለሐና ፀአዳ ርግብ ሰበባቱን ሰማያት ሠንጥቃ መጥታ በራስሽ ላይ ስታርፍ በቀኝ ጆሮሽ ገብታ
በማኅፀንሽ ስታድር አየሁ ብለው ያዩትን ራዕይ ተጨዋውተዋል፡፡ እንዲህ ያለ ራዕይ ካየን ብለው ዕለቱን በግብር አልተዋወቁም ፈቃደ
እግዚአብሔር ቢሆንልን ብለው ለደጅ ጥናት ሰባት ቀን ሰንብተዋል ነሐሴ በገባ ሰባተኛው ቀን በፈቃደ እግዚአብሔር በብስራተ መልአክ
በሩካቤ ዘበሕግ እመቤታችን ተፀነሰች፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ነሐሴ 7 ቀን ከተጸነሰች ጀምሮ በሐና
ማሕፀን ሳለች ብዙ ተአምራትን ማለትም ድውይ
ተፈውስ ዕውር ታበራ ሙት ታስነሳ ነበር፡፡ ከዚያውም ውስጥ ሳምናስ የሚባል የአጎቷ ልጅ ሙቶ ሊቀብሩት ሲሄዱ ሐና ትወደው ነበረና
አልጋውን ይዛ ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት ተነስቶ በማሕፀን እያለች ያስነሳችው እመቤታችንን ሰማይና ምድርን ለፈጠረ እናቱ የምትሆኝ
ሆይ ሰላምታ ይገባሻል ብሎ ሰግዶላታል፡፡ከቅድስት ሐና የምትወለደው የአምላክ እናት እንደሆነች መስክሯል ይህንና ይህንን የመሰለውን
በማድረጓ በተአምራቷ ቀንተው አይሁድ በምቀኝት ሊገድሏቸው ተነሱ፡፡
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ቅዱስ ሊባኖስ ወደተባለ ተራራ ይዘሀት ሂድ ብሎት ‹‹እምሊባኖስ ትወጽእ መርዓት ከሊባኖስ
ሙሽራ ትወጣለች›› እንዲል ‹‹ንኢ እምሊባኖስ ነይ ከሊባኖስ ነይ›› መኃ.መኃ ዘሰሎ 4፤8 እንዲል፡፡ እመቤታችን ግንቦት አንድ
ቀን በ16 ዓ.ዓ በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች፡፡ በልደቷም ሁሉም ተደስተው ስሟንም ማርያም አሏት ፡ ማርያም ማለት ጸጋ ወሀብት ማለት
ነው፡፡ ለጊዜውመ ለእናት ለአባትዋ ጸጋ ወሀብት ሆና ተሰጠታለችና ፍጻሜው ግን ለስው ሁሉ ጸጋ ሀብት ናትና ማርያም አሏት፡፡
ቅድስት ሐና እንደወለደች በሰሙ ጊዜ ዘመዶቿና ጎረበቤቶቿ ዳቦ እየጋገሩ ንፍሮ እያነፈሩ ሌላም ልዩ ልዩ መባልዕትን
እያዘጋጁ ይዘውላት መጡ፡፡ ዛሬም የእመቤታችን በዓል ሲከበር ይህ መንፈሳዊ ልማድ ሲወርድ ሲዋረድ ደርሷልና ይህም ሲፈጸም ይታያል፡፡
በዚህ እለት ዳቦ ጋግሮ ንፍሮ አነፍሮ ጠላ ጠምቆ ጎረቤት ተሰብስቦ ችግረኛን ማብላት ማጠጣት በአንድ ላይ ማዕድን መካፈል የቅድስት
ሐናን በሊባኖስ ተራራ እመቤታችንን መውለድ ማሰብ የሚገባን የሚያበረታታ መንፈሳዊ ልማድ እና ልዩ ልዩ ምግቦችን አዘጋጅቶ ችግረኞችን ማብላትና ማጠጣት በአንድነት
ማዕድን መካፈል የሚደገፍ በረከትን የሚያስገኝ ነው፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም የብጽአት ልጅ ናትና 3 ዓመት ሲሆናት ይህቺ ልጅ አንድ ነገር በብትሆን ከእግዚአብሔርም
ከልጃችንም ሳንሆን እንዳንቀር ሆዷዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ወስደን እንስጥ ብለው መባዕ ጨምረው ወደ ቤተ መቅደስ ይዘዋት
ሄዱ፡፡
ሊቀ ካህናቱ ሕዝቡን ሰብስቦ የምግቧን ነገር ይያዝልኝ አለ ወዲያውም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ኃብስት ሰማያዊ
ጽዋዕ ሰማያዊ ይዞ ረቦ ታየ፡፡ዘካርያስም ለእርሱ ይዞት የመጣ መስሎት ዛሬስ ክብሬን በሰው ፊት ሊገልጠው ነው ብሎ ሊቀበል ተነሳ
መልአኩም ወደ ላይ ራቀበት ፡፡ የእርሱ ምክትል የሆነው ስምዖንም እንኪያስ ለእኔ የመጣ ይሆናል ብሎ ቀረበ መልአኩም ራቀበት፡፡
ካህናቱም ህዝቡም በተራ ቢቀርቡም ራቀባቸው ምናልባት ጥበበ እግዚአብሔር አይመረመርም ለዚች ብላቴና የመጣ ይሆናል ብለው ሐናን ትተሻት
እልፍ በይ አሏት ፡፡ እልፍ ስትል ድክ ድክ እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፍ አንጽፎ አንድ ክንፍን ጋርዶ
በሰው ቁመት ልክ ወደላይ ከፍ አድርጎ መግቧት ዐረገ፡፡ የምግቧ ነገር ከተያዘልንማ ትግባ እንጂ ብለው ከመካነ ደናግል አስገቧት
፡፡ ኅብስት ሰማያዊን እየተመገበች መላእክት እየጎበኟት 12 በቤተመቅደስ
ኖራለች፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ስልሳ አራት አመት (64) ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21 እሑድ ቀን ጌታ እልፍ
አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ አለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት ፡፡ ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህን ዘጠኝ
ወር በማህፀኔ ተሸክሜህ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን አለችው፡፡
በሲኦል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆናቸዋል አልት፡፡ እኒህን ከማርክልኝ ይሁን አለችው፡፡ ቅድስት ነፍሷን
ከክብርት ስጋዋ ለይቶ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀ መዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችንን ቅበሩ
አላቸው፡፡ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ አይተው ልጇ ተነስቷል ብለው አይሁድን ሲያውኩ አሁን ደግሞ እናቱ አረገች ብለው ሊያውኩን ነው ኑ እናቃጥላት ብለው ተነሱ፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ታውፍንያ ዘሎ ያልጋውን ሸንኮር
ያዘ ፡፡ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣዉ፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት ራሷን ዘንበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን
እንደነበር አድርግለት አለችው፡፡
ፍልሰታ ለእግዝትነ ማሪያም
ፍልሰታ መሠረተ ቃሉ ‹‹ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና
የመቅደስህ ታቦት››መዝ 131፡8‹‹ ተንስኢ ወንኢ ሠናይት ርግብየ ውስተ ጽላሎተ ኬክሕ ቅሩበ ጥቅም አቅራቢያዬ መልካሟ ርግብ ተነሽ ነዬ በግንብ አጠገብ ወዳለው ዋሻ ጥላ››መኃ.መኃ 2፡10-14
የሚለው ነው፡፡
ፍልሰታ የሚለው የእመቤታችን ሥጋ ከጌቴሰማኔ ወደ ገነት መፍለሱን ኃላም በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሳቱን ለማመልከት
የሚነገር ቃል ነው፡፡ ሐዋርያት እመቤታችን ካረፈች በኃላ በሀዘን ላይ እያሉ ቅዱስ ቶማስ አልነበረምና ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ
ሲመጣ መላእክት የእመቤታችንን ሥጋዋን ወደ ገነት ሲያፈልሱ አገኛቸው፡፡ ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን
ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁን ብሎ ከልቡ አዘነ እመቤታችን ግን ሐዋርያት ትንሣኤዬን እርገቴን አላዩም አንተ ግን አይተሃል አሁንም ሄደህ
ተነሣች ዐረገች በላቸው ባላ ሰበኗን ሰጠችው፡፡
ሄዶ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ አላቸው፡፡ አግኝተን ቀበርናት አሉት፡፡ ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ለሰሚም
አያምር ተው ይህ ነገር አይመስለኝም አላቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ መጠርጠር ልማድህ ነው አለው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ተቆጥቶ ፊት
ፊት እየሮጠ እነርሱ እየተከተሉት ጌቴሴማኒ ከመቃብሯ ደረሱ፡፡ ቢከፍተው አጣት ደንግጦ ቆመ፡፡ አታምኒኝም ብዬ እንጂ እመቤታችንስ
ተነሣች ዐረገች አላቸው፡፡ ለዚህ ቃልህ ምስክር የሚሆን ምን ይዘሀል አሉት፡፡ በዚህ ሰበን አልገነዛችሁምን አላቸው፡፡ ትንሣኤ ዕርገቷን አምነው ሰበኑን ለበረከት ተካፍለውታል፡፡ዛሬም ሠራዒ ዲያቆኑ በቅዳሴ ጊዜ
በሚይዘው መስቀል ላይ የሚደረገው ጨርቅ የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው፡፡
ነገር ግን ሐዋርያት የእመቤታችንን የዕርገቷን ምሥጢር ለማወቅ ይጓጉ ነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦ ‹‹እናቴን
አሳያችኋለው›› የሚል ተስፋ ሰጥቷቸው ነበር፡፡ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ እርገቷን አይቶ እነርሱ ሳያዩ በመቅረታቸው እያዘኑ የጌታን
ተስፋ ሲጠባበቁ ሳለ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ እመቤታችንን እንዲያሳየን ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረን በጾም ፈጣሪያችንን እንጠይቀው አላቸው
እነርሱም ሐሳቡን ተቀብለው ከነሐሴ አንድ ቀን ጀምሮ ሁለት ሱባኤ ከጾሙ በኋላ ነሐሴ 16 ቀን ጌታ መላው ሐዋርያትን ወደ ገነት
አውጥቶ በገነት ዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረው መቃብር አመቤታችንን ነፍስዋን ከሥጋዋ አዋህዶ አንስቶ ትንሳኤወንና ዕርገቷን አሳይቶ
ለዓለም ይህንኑ እንዲያስተምሩ አዘዛቸው፡፡
እኛም እንደ ሐዋርያት የእርሷን በረከት ለመቀበል ከነሐሴ 1 እስከ 16 ቀን ድረስ ሕጻን ፡ጎልማሳ፡ሽማግሌውም ሁሉ
በመጾም እናሳልፈዋለን ፡፡ የአዟኝቷን ምስጋናዋን ከአንደበታችን ፍቅሯን ከልቡናችን አይለይብን ፡፡ እናትነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን
ማክሰኞ 14 ጁላይ 2015
በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ?(ዘፍ 18÷3
አብርሃም
ማለት አበ ብዙኃን ማለት ነው፡፡ ትውልዱም ከነገደ ሴም ነው አባቱ ታራ ይባላል የአዳም ሃያ አንደኛ ትውልድ ነው፡፡ ቤቱን ከተመሳቀለ
ጎዳና ሠርቶ የወጣ የወረደውን ሰው በእንግድነት ሲቀበል ይኖር ነበር ፡፡ ሰይጣን ከዕለታት አንድ ቀን እራሱን በአብርሃም የተደበደበ
አስመስሎ ከመንገድ ላይ በሰው አምሳል ቁጭ ብሎ እንግዶችን ወዴት ትሄዳላችሁ እያለ ይጠይቃቸው ጀመ ርቦን እንዲያበላን ጠምቶን እንዲያጠጣን
ከአብርሃም ዘንድ ይሉታል፡፡ የድሮው አብርሃም መሰላችሁ እንዴ! እኔም እንደናንተ ርቦኝ ያበላኛል ጠምቶኛል ያጠጣኛል ብዬ ብሄድ
እራሴን ደብድቦኝ አባረረኝ እያለ ሰዎችን ሁሉ ወደ አብርሃምም ያለ እንግዳ አህል አልበላም ውሃም አልጠጣም ብሎ ሰሦስት ቀን ቆየ
በሦስተኛው ቀን በቀትር በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ አግዚያብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍተገለጡለት አይኑንም አነሣና አነሆ ሦስት
ሰዎችን በፊቱ ቆመው አየ፡፡ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነስቶ ሮጦ ወደ ምድርም ሰገደ እንዲህም አለ ገሀሱ አጋዕዝትየ
ቤተ ገብርክሙ ጌቶቼ ከቤት ገብታችሁ እረፊ አላቸው ደክሞናልና እዘለን አሉት አንዱን አዝሎ ሊገባ ሁለቱ በግብር አምላካዊ ገብተው
ተገኝተዋል አብርሃምም ሦስት እንደሆኑ አውቆ ሣራን ሦስት መስፈሪያ ዱቄት ወስደሽ አንድ እንጎቻ አድርገሽ ጋግሪው አላት ሣራም ጋግራ
አቀረበች አብርሃምም ሥላሴን በእንግድነት ተቀበለ፡፡
ትምህርት
·
አንግዶችን
በቤታችን ለመቀበል ዘወትር መዘጋጀት
·
አንዳንዶች
ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋል (ዕብ 13÷1)
·
አንግዶችን
መቀበል ክእግዚያብሔር ዋጋ እንዳለው ማወቅ(ሮሜ 4÷37)
·
አብርሃም
አንግዳ ለመቀበል በረከትን አግኝቷአል መካን የነበረችው ሚስቱ ሣራም ልጅ ወለደች (ዘፍ 21÷1)
መልእክት
አባታችን
አብርሃም ደግ አንግዶች ወደ ቤቱ ካልመጡ እህል የማይበላና ወኃ የማይጠጣ
ሰው ስለነበረ አግዚአብሔር ባርኮታል ዘሩንም እንደምድር አሸዋ አብዝቶለታል፡፡ እኛም አንግዶችን በመቀበል ያለንን በማካፈል ወደ
ኋላ እንዳንል ያጣነውን ፤የምናገኘው ተስፋ የቆረጠን ተስፋችን የሚቀጥለው አይሳካልንም ያልነው የሚሳካው፤ የተዘጋብን የሚከፈትልን
በእምነት ስንኖርና እና እንደ አብርሃም እንግዶችን በመቀበልና በማስተናገድ የምንጠብቀውን ተስፋ በዓይናችን የምናየው በእምነት እየኖር
የእግዚብሔርን እንግዳ ስንቀበል ነው፡፡
የእግዚአብሔርን በረከትም እንዳያልፈን
አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን አሜን!!
ሐሙስ 18 ጁን 2015
“እስመ ለመላእክቲሁ ይኤዝዞሙ በእንቲአከ” መላእክቱ ስለ አንተ ያዝዛቸዋል።(መዝ 90፦11)
ሰኔ
ዐስራ ሁለት በዚህ ዕለት ሚካኤል በኬልቅያ አፎሚያን የምትባል ደግ ሴት ባሏ አስተራኒቆስ ይባላል። ከሀብቷ ከንብረቷ እየመጸወተች
በጾም በጸሎት ተወስና ትኖር ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያፍርምና ደግ መነኩሴ መስሎ አጋንንትን መነኮሳይት አስመስሎ መጥቶ ከደጅ ሆኖ አስጠራት ከቤት ገብታችሁ በቅዱስ ሚካኤል
ስዕል ፊት ጸልዩልኝ አለቻቸው እኛማ በነግህ ጸልየናል እንደው አንቺ ይህ ሁሉ ጾም ጸሎት ምን ያደርግልሻል? ሲበዛ ያለጊዜ አንደ
ሚጐዳ አታውቂምን ; ሀብትሽን ሰጥተሸ መጨረሻሽ ምንድ ነው ስትደክሚ የሚረዳሽ የሚጦርሽን ልጅ የለሽ ሁለተኛ ማግባት ኃጢኣት መስሎሻልን
እነ አብርሃም እነ ዳዊት ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች ወልደዋል አሁን ባል አግቢ እኔ የምልሽን እሽ በይኝ አለ “ ኦ አባ አስኬማከ
ሠናይ ወቃልከሰ አኩይ” አባ ቃልህ መልካም ነበረ ንግግርህ ግን ክፉ ነው፡፡ አለችውና በሏ በሕይወት እያለ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤል ስዕል ካስቀመጠችበት አውጥታ ብታሳየው ሰኔ 12 ቀን
መጥቼ ከተመካሽበት ከዚያ ሰዕል ጋር አጠፋሻለሁ ብሏት እንደ ትቢያ በኖ ጠፍቷል፡፡ ሰኔ 12 ቀን የብርሃን መልአክ መስሎ መጥቶ
ጾም ሸሎትሽ ስግደትሽ፤ ምፅዋዕትሽ፤ አርጎል፡፡ ላድንሽ መጥቻለሁና ስገጅልኝ አላት አንተ ማንህ? አለችው የመላእክት አለቃ ቅዱስ
ሚካኤል ነኝ አላት የንጉሥ መልእክተኛ ያለማኀተም ይሄዳልን በተረ መስቀልህ ወዴት አለ አለችው እርሱም መልሶ መስቀል አሲዞ መሳል
ልማድ ነው እንጅ እኛ መላእክት አንይዝም አላት ቆየኝ/ጠብቀኝ/ ስዕሉን ላምጣልህ ብላ ወደ ቤቷ ዘወር ስትል መልኩን ለውጦ ጨለማ
መስሎ ታያት ቅዱስ ሚካኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ መጣ አፎምያን እረድቶ ጾምሽ፤ጸሎትሽ ስግደት፤ ምጽዋትሽ ቅድመ እግዚአብሔር ደርሷል
ዕረፍትሽ ዛሬ ነው፡፡ ብሏት ከሷ ተሰወረ ወደ ቤተክርስቲያን ሄዳ ሥጋውንና ደሙን ተቀብላ ገንዘቧን ሁሉ መጽውታ በዚህ ዕለት በክብር
አርፋለች፡፡
ሁለተኛው በዚህ ዕለት የሚከበረው ባሕራን ነው
ሀገሩ እስክንድሪያ ነው ወላጆቹ
የቅዱስ ሚካኤልን በዓል እያከበሩ ይኖሩ ነበር፡፡ ባሕራን ተጸንሶ ሳለ አባቱ ሞተ ባሕራን በተወለደ ጊዜ ሕፃኑን የመላእክት አለቃ
ቅዱስ ሚካኤል ባረከው የዚህ የጎረቤትሽን የባለ ጸጋ ሐብት ይወርሳል ሲላት ባለ ፀጋው ጎረቤቷ ሰማ ነገሩን ከልቡ ሲያወጣ ሲያወርድ
ቆይቶ ባሕራንን ዐሥር አመት ሲሆነው እናቱ የምታብሰው ቆርሳ የምትሰጠው አጥታ በጣም ተቸገረች ባለፀጋውም እኔ ወስጄ ለምን አላሳድገውም
አላትና ለርሷ ሃያ ወቄት ወርቅ ሰጥቶ ወሰደው ወድያውም ሳጥን አሰርቶ በአሰራው ሳጥን ከቶ ከባህር ጣለው ማዕበል እየገፋ ወስዶ
ከወደቡ አደረሰው አንድ በጎቹን የሚጠብቅ እረኛ አገኘው ከነጋዴ የወደቀ እቃ አገኘሁ ብሎ ከቤቱ ወስዶ ቢከፍተው መልከ መልካም ልጅ
ይፈልግ ነበርና በጣም ደስ አለው ስሙንም ባሕራን ብሎ ጠራው ከባሕር የተገኘ ሲል ነው፡፡ ከበላው እየበላ ከጠጣው እያጠጣ አሳደገው
ከብዙ ዓመታት በኋላ ባሕር ላይ የጣለው ባለፀጋ ለንግድ ሲሔድ መሽቶበት ባሕራንን ባሳደገው ቤት አደረ ባሕራን ባሕራን እያለ ሲጠራው ባሕራን ማለት ምን ማለት ነው አለው፡፡ ከባሕር የተገኘ ማለት
ነው መቼ አገኘኸው አለው ጊዜውን ጠቅሶ ሲነግረው በልቡ ለካ አልሞተም አለ ሲነጋ ከቤቴ የረሳሁት እቃ አለና እባክህ ፍቀድልኝ ልጅህን
ባሕራንን ልላከው፡፡ የድካሙን ዋጋ ለአንተ እከፍላለሁ አለው፤እሽ አለ እንደ ደረሰ ግደሉት ብሎ ደብዳቤ ጽፎ አትሞ ምልክት ነግሮ
ስንቁን አስይዞ ላከው ዘጠኝ ቀን በእግሩ ተጉዞ የአንድ ቀን ጎዳና ሲቀረው ቅዱስ ሚካኤል በአምሳለ ሐራ በፈረስ ተቀምጦ መላእክት
እንደ ሠራዊት አስከትሎ ከመንገድ ላይ ተገናኘው አንተ ጎበዝ ወዴት ትሔዳለህ? መላእክት ተልኬ ለደርስ እየሄድኩ ነው፡፡ ብሎ መለሰለት
እስኪ መልእክቱን አሳየኝ አለው ባሕራንም ደብዳቤውን አሳየው፡፡ እፍ ቢልበት የሞቱን ትዕዛዝ አጥፍቶ የሕይወት ትዕዛዝ ጽፎበታል፡፡
ደብደቤውን ለቤቱ ሹም ሰጠው ቢገልጠው ልጄን ለላኩት ሰው ዳሩለት ሐብት ንብረቱን አውርሱት ባሮቼ ይገዙለት የሚል አነበበ ባሕራንም
የባለጸጋውን ልጅ አገባ ባለ ጸጋውም ከንግድ ሲመለስ የዘፈን ጨዋታ ድምፅ ሰምቶ የምሰማው ድምፅ ዘፈን ጨዋታ ምን ተገኝቷል?፡፡የላከው
ሰው ልጅህን አግብቶ ሐብትህን ወርሶ ይኸው አርባ ቀን ሙሉ ይዘፈናል አለው ወዲያው ደንግጦ ከፈረሱ ወድቆ ሞቶአል ባሕራንም የባለፀጋውን
ሐብት ወርሶ አግዚአብሔርን አያመሰገነ ቅዱስ ሚካኤልንም እያከበረ ኖረ፡፡
ትምህርት
- እግዚአብሔር መልእክትን በመንገዳችን እንደሚልክልን (ዘጸ23፡-20)
- መልካም ሥራችን አንደማንወድቅ(መዝ.40፡-1)
- የጾምና የጸሎት የምጽዋት ጠቀሜታን(የሐዋ.9፡-31)
- የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት እንደሚቀየር ማመን(መ.አስቴር 7፡-9)፡፡
መልእክት
በደግነትና በመልካምነት የታወቀችው
አፎምያና በባሕር ውስጥ ተጥሎ የተገኘው ባሕራን በዚህ ዕለት አምላካችን አግዚአብሔር መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልን ልኮ ከጠላት ታድጎቸዋል፡፡
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)





