v
“በልዑል
ዙፋን ላይ ተቀምጦ ያለ እርሱ በበረት ተጣለ፣ ስጋ ሳይሆን የነበረ የማይዳሰስ ወልድ ዋህድ ዘሬ ስጋን በመዋሃድ ተዳሰሰ፣ሃጥያትን
ይቅር የሚል ራሱ በጨርቅ ተጠቀለለ” (ሃይማ.አበው ዘዮሐንስ አፈወርቅ)
v
“ኦ
ለዝንቱ መንክር ልዑል…”ከህሊናት ሁሉ ለላቀ ለዚህ ድንቅ ምስጥር አድናቆት ይገባል፤ምድራዊት ሴት ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃልን
ወለደችው፤ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው፤እርሱም እናቱን ፈጠረ፤ከእርሷም እርሱ የፈጠረውን ስጋ ተዋሐደ በእኛ ባህርይ ተወለደ እርሱም
እኛን ስለመውደዱ ፈጠረን በእኛ ባህሪይ ወለደችው ፈጣሪም እንደሆነ ታወቀ፡፡(ቅ.ያዕቆብ ዘስሩግ)
v
“ዳያቢሎስ
በልደት ማየት የተሳነውና ያስደነገጠው ብርሃን፤ዳግመኛም በዕለተ አርብ በብርሃን ነጸብራቅ ኃይል የጨለማውን አበጋዝ እውር ያደረገው
ይህ ማን ነው፤ወገኖቼን እገዛ ዘንድ ያልተወኝ ይህ ማን ነው? ነገር ግን ተሰጠተውኝ የነበሩት ነፍሳትን ሁሉ ወደሰማይ ያወጣል እንጂ
በማለት ፍጹም ሽንፈቱን ገልጾታል፡፡ ”(ትምህርተ ኅቡአትን ተመልከቱ)
v
#ዲያብሎስ በስጋ ከይሲ ተሰውሮ አዳምን ድል በነሳው ጌታ ድግሞ
በጥበብ በስጋ ብእሲ ተሰውሮ ዲያብሎስን ድል ነስቶታል;(መቅድመ ወንጌል)
v
“ጌታ
ሲወለድ በቤተልሔም ብርሃኑ ሲያበራ ሰይጣን እየተቻኮለ ከሰፈሩ በወጣ ጊዜ ክፉዉ ጭፍራ በጸጥታ ቆሞ ይጠብቀው ነበር፤ራሱም በርሮ
ወጣ ወደ ከፍታዎችና ወደ ዝቅታዎችም ሁሉ ፈጠነ በሁሉም ክልሎችና ድንበሮች አለፈ፡፡ከሩቅ ሆኖ ወደ ቤተልሔም አቅጣጫ ተመለከተ አንድ
መልኣክም በአስደናቂ ክብር የብርሃንንም ጸዳል ተላብሶ፤እየበረረ ሲዞር ሲመላለስም፤በደስታ ተመልቶ እና እየፈጠነ፤ውብ እና አስደሳች
ሆኖ አሳቱ እጅግ እያበራ ከድምፁም ታላቅ ብርሃን እያመነጨ ሲያልፍ አየ፤ሰይጣንም አይቶት በፍርሃት እየራደ ተሸሸገ፡፡”(በቅዱስ
ያእቆብ ዘስሩግ ድርሳን)
v
ቅዱስ
ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ላይ “ትእምርተዋሕዱ ረሰየኪ አብ”አብ የራሱ ምልክት አደረገሽ አለ እርሱ ቅድመ ዓለም ያለ እናት፤አንድም
ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአንድ ልጅ ምልክት አደረገሽ አለ እሷ ድንግልወእም (ድንግልም እናትም) ስትባል መኖሯ ራሱም አምላክወ
ሰብእ (አምላክም ሰውም) ሲባል የመኖሩ፤እርሷም ስትወልደው ማኀተመ ድንግልናዋ አለመለወጡ እርሱም ሰው ሲሆን ባህርየ መለኮቱ ያለመለወጡ
ምሳሌነት በማለት ምሳሌነቱትን አስቀምጦል፡፡

