በስመ አብ ወወለወድ
ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
“ ሕፃን ተወልዶልናልና”
ልደታት
ብዙ አሉ ፡፡ ልደተ አዳም ከምድር ልደተ ሔዋን ከአዳም ፣ልደተ ሙታን ከመቃብር ልደተ ሕፃናት ከእናታቸው ማህፀን የሚጠቀሱት ናቸው፡፡የእነዚህ
ሁሉ ልደት ለራሳቸው ኢነጂ ለእኛ አይደሉም “ህፃን ተወለልዶልናል የሚለው ግን ለእኛ ነው፡፡”የአምላክን መወለድ ብዙ ነቢያት በብዙ
ሕብረ ትንቢት ተናግረዋል በብዙ ሕብረ አምሳል መስለዋል፡፡”ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ አይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ዳግምም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ
በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን “ ዕብ1፣1 በብዙ ሕበረ አምሳል በብዙ ሕብረ ትንቢትእግዚአብሔር ከተናገረባቸው ነቢያት አንዱ
ኢሳይያስ ነው ኢሳይያስ ከነቢያት ወንድሞች በተለየ መልኩ የአምላክን ሰው መሆን የተናገረ ነቢይ ነው ፡፡መወለዱን፣ስሙን፣ከማን እነደሚወለድ
፣ለሰው ልጆች ያደረገውን የቤዛነት ስራ መከራ መቀበሉን ፣በጎል መወለዱን በግልፅ ከተናገሩ የተነሳ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያ ወንጌላዊ
ነቢይ የሚል ቀጽል ሰጥተው ይጠሩታል፡፡የትንቢት መጽሐፉንም ደረቅ ሐዲስ በማለት ሰይመውታል፡፡ይህም ማለት ስለክርስቶስ መወለድ በምሰሌ
ያይደለ በቀጥታ የተናገረ በመሆኑ ነው ለምሳሌ የሚከተሉትን ማየት
ይቻላል፡፡
“ጌታ
ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች”ኢሳ 7፣14 ከላይ ባጭሩ
እንዳየነው ከማን እንደምትወልድ ስሙን ማን አንደሆነ በግልጽ እስቀምጸጧል ፡፡ኢሳይያስ ቃል በሉቃ 1፣26 የምናየው ነው ፡፡በስድስተኛው
ወር ገብርኤል መላክ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ ከዳዊት ወገን የሆነ ስሙ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ከታጨች ከድንግል
ዘንድ የዚህች ድንግል ስሟ ማርያም ነው” በማለት ወንጌለዊው ገልጧል “በነቢይ ከጌታ ዘንድ እነሆ ድንገል ትፀንሳለች ወንድ
ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለውን ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው
ማቴ 1፣22 ኢሳይያስ “ሕፃን ተወልዶልናል”ብሎ ለእኛ መዳን የተወለደው ነገረን ቀጥሎም ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል “ ይላል ሥጋውን
በልተን ደሙን ጠጥተን መድኃኒት ለሆነን እንደመጣ ሊያሳይ ፡፡ ከዚህ በመቀጠል እርሱን ለመግለጥ የተጠቀማቸው ቃላት በጣም የሚደንቁ
ናቸው፡፡
1.
ስሙ
2.
ድንቅ
3.
መካር
4.
ኃያል
5.
አምላክ
6.
የዘላዓለም አባት
7.
የሰላም አለቃ
በሚሉ
ሰባት ቃላት ገልጾታል ቁጥሩ በእብራዊያን ዘንድ ፍጹም ነው ከላይ ኢሳይያስ የተጠቀማቸው ሰባት ቃላት ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑን
የሚያስረዱ ናቸው ፡፡ሕፃን ብሎት ነበር ሕፃን የሚለው ስም ታህታዊ ማንም በሥጋ የወለደ ሰው ሲወለድ የሚጠራበር ነው ፡፡ ሰው መሆኑን
ለመግለጥ ሕጻን አለው አምላክነቱን ለማስረዳት ስሙም ብሎ ጀምሮ በሰባት ቃለት አስረድቶናል፡፡
1.
ስሙ
ስለ
ስሙ ቅዱሳት መጻፍት ሲናገሩ ኢየሱስ ፣አማኑኤል፣ ክርስቶስ ፣መድኃኔዓለም የሚባሉት ስመ ስጋዌ ናቸው ሰው በመሆኑ የተጠራባቸው ኢየሱስ
ማለት መድሐኒት ማለት ነው፡፡ አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው ከእኛ ጋር ሲባል ከስጋችን ሥጋ ከደማችን ደምን
ነስቶ ሰው የሆነ አምላክ ማለት ነው ክርስቶስ ማለት መሲህ ፣ሹም፣ንጉሥ ፣አለቃ ማለት ነው፡፡ መድኃኔዓለም ማለት የአለም መድኃኒት የዓለም ቤዛ ደሙን አፍስሶ ሥጋውን ቆርሶ በደሙ ዓለምን የዋጀ ማለት ነው፡፡
“ልጅም ትወልዳለች እርሱም ሕዝቡን ከኃጢያታቸው
ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለች” ማቴ 1፣21
“ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ እርሱ
በመጣ ጊዜ ሁለን ይነግረናል አለችዉ ኢየሱስም የምትናገሪዉ እርሱ እኔ ነኝ አላት”ዮሐ 1፣42
“እኛ ራሳችን ሰምተነዋል አርሱም በእውነት ክርስቶስ
የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን “ዮሐ 4፣42
ከላይ
የተመለከትናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስሙንና ግብሩን የሚገልጡ ናቸው፡፡ትርጉሙ ከተግባር ጋር የተያያዘ ነውና ይህንን ነው ኢሳይያሰ
“ሕፃን ተወለደልን” በማለት የተነገረለት ኢሳይያስም ሕጻን ብሎ የጠራዉ ሰዉ ሲሆን አምላክነቱ አልተለወጠምና አምላክነቱን መግለጥ
የሚችሉ ቃላት ከስሙ ጀምሮ ተጠቅሟል
ስሙ አዳኝ ነው፡- አቤቱ በስምህ አድነኝ መዝ
53፣1
ስሙ ቅዱስ ነው፡- እርሱ ለእኔ ታላቅ ስራ አድርጎል
እና ስሙም ቅዱስ ነው ሉቃ 1፣50
ስሙ ፡- አጋንንትን ይገዛል “አጋንንት በስምህ
ተገዙልን” ሉቃ 10፣17
ያመኑትን እነዚህን ምልክቶች ይከተሏቸዋል በስሜ አጋንትን ያወጣሉ እባቦችን ይይዛሉ የሚያሰክር መርዝ ቢጠጡ አይገድላቸውም ማር 16፣17
ስሙ፡- ስግደት የሚገባው ነው “እግዚአብሔር/እግዚአብሔርነቱ/
ያለልክ ከፍ ከፍ አድርገው ከስምም ሁሉ በላይ ያለዉን ስምሰጠው ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ
ስም ይንበርከኩ ዘንድ”ቆላ 2፣9-11
ስሙ ምስጋና ይገባዋል”በሰማያት የምትኖር አባታችን
ሆይ ስምህ ይቀደስ”ማቴ 6፣9
2.
ድንቅ
ድንቅ ማለት ቃል እነደሚገባው አድርጎ የማይገልጠዉ
ቃላት ላጣንለት ነገር የምንጠቀመዉ ነዉ በህቱም ድንግልና ተጸንሶ በህቱም ድንግልና መወለዱን ሲደንቅ የሚኖር ነውና በኪሩቤል ላይ
የሚገለጥ ስጋን ለብሶ መወለዱን የማይወስነዉ መወሰኑ የማይዳሰሰው መዳሰሱ የማይታየው መታየቱ የማይጨበጠው እሳተመለኮት በጨርቅ መጠቅለሉ በጎል መጣሉ የሚደንቅን ነው እነኳን
ለኢሳይያስ ለመላእክትም ድነቅ ነው ሰማይ ዙፋኑ የሆነ አምላክ በትህትና መገለጡ ድሆች እንኳ ባልተወለዱበት የከብቶቸች በረት መወለዱ
ድንቅ ነው፡፡
“በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ”እግዚአብሔርን
ስራህ ድንቅ ነው በሉት መዝ65፣3 ሕፃናትን በእናታቸው ማህጸን የሚጠብቃቸው ሕጻን ሆነ ይህ
እንዴት አይደንቅ
“ስራህ ድንቅ ነው
ነፍሴም እጅግ ታዉቀዋለች” መዝ 138፣12 በላይ በሰማይ በኪቤል ጀርባ በምድር በእናቱ እቅፍ መታየቱ ድንቅ ነው?
“ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ ለዓይናችን
ድንቅ ነው” መዝ 117፣22 ማቴ 22፣42
3.
መካር
ሰው ለመሆን መወሰኑን በልብ የመከረውን በነብያት ያናገረውን ያን የፈጸመ ምክረ
ከይሲን በምክሩ የሻረ ዲያብሎስን ያሣፈረ በልቡ ጥበብ ከሰው ልጆች በተለየች ምክሩ አዳምን ነጻ ያወጣ መካር ነው፡፡”ግሩም ምክሩ
እምጎለመኸያው”ምክሩ ከሰው ልጆች ይልቅ ልዩ ነው “መዝ 65፣5 በዚህ
በልዩ ምክሩዲያብሎስ የመከራቸውን የነፍስና የስጋ ተዋህዶ በሥጋ ተወለደ ይህ የዲያብሎስን ስራ ያፈርስ ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅ
ተገለጠ 1ተሰ3፣7
“ውዕቱ ጥበቡ ወምክሩ ያድኅነነ መጸአ “ እርሱ የአብ ጥበቡና ምክሩ ሊያድነን መጣ” ይለዋል ቅዱስ ያሬድ
4.
ኃያል
ኃያልነት የበሕርይ ገንዘቡ ነው
“ኀይሉ ለአብ ወጸጋ ለአህዛብ…”የአብ ኃሉ እርሱ ነው ለአህዛብም ጸጋን የሚሰጥ “ እነዳለ መጽሐፈ ኪዳን ፡፡ መንግሥትህ ያንተ
ናትና ኃይል ምስጋና ክብር ለዘላለሙ” ማቴ 6፣13 በኃይሉ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃዉን ሊነጥቀዉ እንዴት ይቻላል ማቴ12፣29
“ክርስቶስም ስለ አናንተ አይደክምም
/ደካማ /አይደለም ነገር ግ ን በእናንተ ኃለኛ ነው በድካም ተስቅሏልና ነገር ግን በእግዚአበሔር /በእግዚአብሔር/ኃይል በሕወት
ይኖራል 1ቆሮ 13፣3-5
“የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው
ክርስቶስ ነው” 1ቆሮ 1፣24 -26 ሰዎች ይህንን የእግዚአብሔር ኃይል አላወቁም ነበር “ የእግዚአብሔርን ኃይል አታዉቁም እና
ትስታለችሁ” ማቴ 22፣22
5.
አምላክ
ክርስቶስ አምላክ ነው እግዚአብሔር
ነው ኢሳይያስ ሕጻን ካለው በኋላ አምላክ ብሎታል “የእግዚአብሔር ስራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ እርሱ ወይም ወላጀፐቹ ኃጢአት
አልሰሩም “ ዮሐ 9፣3 “ያቃልም እግዚአብሔር ነው ዮሐ 1፣1 ሥጋ የለበሰው ሕጻን የተበለው እርሱ ነው እርሱ የሁሉም
ፈጣሪ ነው ፡፡ “ሁሉ በእርሱ ሆነ ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ “ዮሐ 1፣3 “ቃል ሥጋ ሆነ “ ዮሐ 1፣14 ሥጋ ሆነ ማለት ሰው
ሆነ ተወለደ ማለት ነው “ጌታዬና አምላኬ “ ዮሐ20”እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሳ “መዝ 77፣65 “እግዚአብሔር በእልልታ
አረገ”መዝ 46፣5 የሚሉት የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት ይመሰክራሉ፡፡እሳይያስም አምላክ ያለው የወረደው የተወለደው ህጻን የተባለው
ያረገው ክርስቶስ ነው፡፡ ፈጣሪነቱ “በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን”ኤፌ 2፣20 ፈጣሪ ካልሆነ ሊፈጥር ይችላልን ?”በሰማይም በምድርም ያሉ ለእርሱ
በእርሱ ተፈጥረዋል” ቆላ 1፣16 “በስጋ ጠተገለጠ በመንፈስም የጸደቀ (የባህርይ አምላክነቱ የታወቀ) ለመላእክት የታየ
ለአህዛብ የተሰበከ በዓለም የታመነ በክብር ያረገ” 1ጢሞ3፣16 የሚሉት
አምላክነቱን ሰው መሆኑን መገለጡን መወለዱን መታመሙን በክብር ማረጉን ያሳየናል ስለዚህ ኢሳይያስ ሕጻን አለው የባሕርይ አምላክ ነውና፡፡
6.
የዘላዓለም አባት
ክርስቶስ አምላካችን ነው ፡፡
አባታችን በፈጣሪነቱ አምላካችን በቸርነቱ አባታችን ነው የመጀመሪያ አባታችን አዳም ለዉድቀታችን ምክንያት ሲሆን ሁለተኛው አባታችን
ክርስቶስ አነሳን ስለዚህ አባት ልዩ መሆኑን እንገነዘባለን ፡፡የሥጋዊ አባት በሥጋ ይወልዳል በበወተት በፍትፍ ያሳድጋል የሚያልፍ
ርስት አዉርሶ ይሞታል ክርስቶስ ግን ሲወልደን በርቀት ሲያሳድገን በስጋውና በደሙ የሚያወርሰንም የማታልፈዉን መንግሥት ነው ፡፡የዘላለም
አባት አባት አለው፡፡ ይህንን እርሱ ባለቤቱ አጽድቆታል “እናንተስ በምትጸልዩበት ጊዜ እንዲህ በሉ በሰማያት የምትኖር አባታችን”ማቴ
6፣9
“ሀግነ ቀዳማየ አበ ዘውእቱ
አዳም ወቦቱ ማሰነ ወተለዉነ አበ ዓለም ሀዲስ””የጠፋንበት የመጀመሪያ አባታችን አዳምን ተዉን አዲስ የዓለም አባት ከርስቶስን ተከተለልን
ሃይ.አበ ስለዚህ አባት ብሎታል አሳይያስ፡፡
7.
የሰላም አለቃ
ሰላምን በመወለዱ የመሠረተ ያጸና
እርሱ ነውና የሰላም አለቃ አለው “በተወለደ ጊዜ ሕጻን በሆነበት ሰዓት ከመላእክት የተሰማው የምስጋና ድምጽ ይኸው ኢሳይያስ ያለው
ነው
“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት
ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብዕ””በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስጋና ሠላም በምድር ለሰው ልጆች “ሉቃ 2፣1 ህዝብና አህዛብን በምስጋጋና
በሃይማኖት አንደ ያደረገ እርሱ ነውና የሰላም አለቃ ብሎታል በዓለም ሁሉን ያስተባበረ ሰላም ተገኝቶ አያውቅም አንዱ ሰላም ሲያገኝ
ሌላው ሰላም ያጣል ከርስቶስ ግን ሰላምን ለሁሉም በአንድ ጊዜ የሰተ የሚሰጥ ነውና የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፡፡ ሰላምን የሚሰጥ
የሚይዝ ማለት “ወሀቤ ሰላም መድኃኔዓለም “ መጠሪያው ሰላም ሰጪ ተብሎ ነው ፡፡
“ሰላሜን እሰተሰጣችኋለሁ እኔ
የምሰታችሁ ሰላም ዓለም አንደሚሰጣችሁ ኤይደለም “ዮሐ 14፣27 “ሰላም ለሁላችሁ ሁን “ ብሎ ሰላምን ለሁሉ የሰጠ እርሱ ብቻ ነው
ዮሐ 20፣26 በክርስቶስ ልደት ዓለም ያጣውን ሰላም አግኝቷል፡፡
ይቆየን

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ