~››› እነሆ ሐጢያትን የሚያስተሰርይ የእግዚአብሔር በግ እያለ ጮኸ ~ ልዑል ሲሆን ትሁት ሆነ በባሪያው እጅ ተጠመቀ
የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል እኔ በውሃ አጠምቃኋለው እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል እያለ ስለ ክርስቶስ መሰከረ ይህንንም እየመሰከረ ሳለ ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንጦስ ፆምን ከመጀመሩ አስቀድሞ ወደ ዬርዳኖስ መጣ ። ዪሐንስም እየሱስ ክርሰቶስን ሲያይ ‹‹ እነሆ ሐጢያትን የሚያስተሰርይ የእግአብሔር በግ›› እያለ ጮኸ ይኸውም ከእኔ ቡኃላ ይመጣል ከእኔም በፊት ነበረ ከእኔ ይልቅ የከበረ እርሱ እየሱስ ነው እያለ መሰከረ፡፡ ራጉኤል በትጋቱ እዬብ በፅድቁ አባቶች በስራቸው የሚያቃጥለውን እሳተመለኮት ጌታን ማጥመቅ አልተቻላቸውም ዩሐንስ ግን አጠመቀው።
ልዑል ሲሆን ትሁት ሆነ በባሪያው እጅ ተጠመቀ፤ የክርስቶስ ነገር እጅጉን ይገርማል ይደንቃል። አንድ ጊዜ ኃጢአትን የሚያስተሰርይ ስለእኛም መስዕዋት የሆነ እውነተኛ የእግዚአብሔር 'በግ'፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ 'የበጐች ቸር እረኛ'። አንድ ጊዜ ሀጢያት እንዳለበት ሲጠመቅ እናያለን ሌላ ጊዜ ደግሞ አንቺ ሴት ሀጢአትሽ ተሰረየ እያለ ከማዕሰረ ሀጢአት ሲፈታ እናያለን፤ አንድ ጊዜ ሳምራዊቷን ውኃ አጠጪኝ እያለ ይለምናል ሌላ ጊዜ ደግሞ የማይደርቅ ምንጭ የህይወት ውኃ እርሱ ነው፤ አንድ ጊዜ 'ተራበ' ይለናል በሌላ ጊዜ ደግሞ አለምን የሚመግብ እርሱ እንደሆነና ህብስቱን አበርክቶ ሲመግብ እናያለን፤ አንድ ጊዜ ድካም የሌለበት ብርቱ ሆኖ እናንተ ሽክማችሁ የከበዳችሁ ወደእኔ ኑ እኔም ከድካማችሁ አሳርፋችኁአለሁ ይላል በሌላ ቦታ ደግሞ ሰው እንደመሆኑ 'ደክሞት አረፈ' ይለናል፤ አንድ ጊዜ አይሁድ እንደያዙት እንዳሰሩት እንዳደከሙት እንደሞተ እናያለን ሌላ ጊዜ ሁሉን የሚይዝ ከኃጢአት ማሰሪያ የሚፈታ ሀያል ብርቱ ሆኖ ሞትን ድል እንደነሳ እናያለን፤ ስለዚህም 'ሁሉን የሚዘውን ያዙት ከማዕሰረ ኃጢአት የሚፈታውን አሰሩት እንዳለ'። አንድ ጊዜ በስሜ አጥምቁ ይላል ሌላ ጊዜ ደግሞ ሊጠመቅ ወደ ባህር ይወርዳል፤ አጥማቂ ሊቀካህን ሲሆን የኛን እዳ በደል ሊሽር ተጠመቀ፤ ልዑል ሲሆን ትሁት ሆኖ በባሪያው እጅ ተጠመቀ።
ዮሐንስ ግን ባሪያ በጌታው እጅ ይጠመቃል እንጂ ጌታ በባሪያው እጅ ይጠመቃልን? እኔ ወደ አንተ ልመጣ ይገባል እንጂ እንዴት አንተ ወደ እኔ ትመጣለህ? አህዛብን ሁሉ ባንተ ስም ሳጠምቅ ነበር አንተን ግን በማን ስም አጠምቅሀለሁ ? እያለ ሊከለክለው ወደደ፤ ክርስቶስ ግን 'አንተ ካህኑ ለአለም በከመ ሲመቱ ለመልኬtsዴቅ ' ብሩክ የእግዚአብሔር ልጅ ማረን ይቅር በለን እያልክ አጥምቀኝ አንተም መጥምቀ መለኮት ተብለህ ክብርህ ይነገራልና እኔም በባሪያው እጅ ተጠመቀ ተብሎ ትህትናዬ ይነገራልና ጽድቅን ሁሉ እንፈጽም ዘንድ ይገባልና ብሎት ተጠምቁአል።
እኛንም ከበደላችን ያነፃን ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ ለተጠመቀ ለእርሱ ምስጋና ይገባል ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
