ትምህርተ ሃይማኖት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ትምህርተ ሃይማኖት
መግቢያ
ሃይማኖት ሰው በራሱ ፈቃድ በመፈላሰፍ የሚያገኘው ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ የተመሰረተ በልቡና በማመን ይሆንልኛል፣ይደረግልኛል፣ በማለት የሚቀበሉት፣ሰውና እግዚአብሔር የሚገናኙበት መንገድ ነው፡፡ በዚህ ዘመን የተለያዩ ሰዎች ለሥጋዊ ፈቃዳቸው እንዲመቻቸው የሚመሠርቱትን የኑሮ ፍልስፍና ሃይማኖት ብለው ሲጠሩት ይታያል፡፡ ነገር ግን ሃይማኖት በእግዚአብሔር መለኮታዊ ፍቅር ላይ የተመሰረሠረተ፣ በራሱ በእግዚአብሔር መገለጥ ጥበብ የታወቀ፣ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን በመንፈሳዊ ጥበብ የሚመረመር በመሆኑ ልዩ ነው፡፡ በመሆኑም ሃይማኖት እግዚአብሔርና ሰዎች የሚገናኙበት ብቸኛ መንገድ ነው፡፡           
  ሃይማኖት ማለት ምን ማለት ነው?
ሃይማኖት  አምነ-አመነ /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ላይ ያለው ሙሉ ማብራሪያ ይመልከቱ/ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ማመን፣ ይሆንልኛል፣ ይደረግልኛል ብሎ መቀበል፣ለእግዚአብሔር የሚሳነው የለም በማለት ሳይጠራጠሩ መቀበል ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ሃይማኖት፤
@ እግዚአብሔር ከሰውና ከመላዕክት ጋር የሚገናኝበት መሰላል ነው
@ በስሜት ሕዋሳታችን የማንደርስባቸውን የሚያስረግጥ ነው
@ እግዚአብሔር የሚገኝበት መንገድ ነው
@ እግዚአብሔርን ደስ የምናሰኝበት ነው
@ የአጋንንትን ፆር የሚከላከሉበት መሳሪያ ነው
@ ክፍዎች የማይሄዱበት የሕይወት ጎዳና ነው
@ ሕይወተ ሥጋና ሕይወተ ነፍስ የሚገኝበት ነው
@ የዘለዓለም አክሊልን የሚያቀዳጅ ነው፡:
ከላይ የተጠቀሱት የሃይማኖት ትርጉሞች እንዳሉ ሆነው ዓለም አቀፍ የነገረ መለኮት ምሁራን ሃይማኖትን ዶግማ ይሉታል፡፡              

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ