ትምህርተ ሃይማኖት፣ነገረ-ማርያም፣ነገረ-ቅዱሳን፣ኪነጥበብና ስብከቶች የሚቀርብበት ገጽ ነው፡፡
እሑድ 13 ሴፕቴምበር 2015
የኮ/ደ/ብ/ቅ/ሥላሴ ቤ/ክ አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ሃይለ ማርያም መንገሻ የአውደ ዓመት መልካም ምኞትና መልዕ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
አዲሱ አመት የሰላም፣የፍቅር፣ የዕውቀት፣ የልማት፣ የእድገት ፣የትምርህት፣
የስራ፣ የብልጽግና፣የጤና ዘመን እንዲያደርግልን እግዚአብሔር እየተመኘሁ፡፡
የአባቶቻችን የቀናች ሃይማኖት
ቅድመ
አለም ከነበረው ዓለምን ከፈጠረው እግዚአብሔር አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ከሦስት አካል አንዱ እግዚአብሔር ወልድ ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በተለየ አካሉ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ተወለደ፡፡
ይህ ቅድመ
አለም የነበረው ከድንግል ማርያም የተወለደው እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህርይ አንድ
ባህርይ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነው ብሎ በምስጢረ ተዋህዶ ማመን ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ እምነት ነው፡፡
ቀዳማዊ
ደሐራዊ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከባህርይ አባቱ ከአብ ከባህርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ አለም ሳይፈጠር የነበረ ሲሆን
ያለ እርሱም ምንም ምን አልተፈጠረም እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ዩሐ.፩፣ ፩-፲
ቃለ እግዚአብሔር
ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ያለዘርዐ ብእሲ ሲወለድ የቅድስት ድንግል ማርያም ማህተመ ድንግልና አልተለወጠም እመቤታችን ድንግል
ማርያም ድንግል ወእም ድንግል ሳለች እናት እናት ሳለች ድንግል ናት፡፡
ስለ ምስጢረ
ድህነት ትምህርት ሲነገር የምስጢረ ድህነት መነሻዋ ድንግል ማርያም ናት ይኸውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ያዳነው ከድንግል
ማርያም በነሳው ሥጋ የሰው ዘርን በመውደዱ እስከ ሞት ድረስ ባደረገው ካሳ ነው፡፡
ቅዱሳን
አበው ሐዋርያት ያስተማሩት የቤተክርስትያን ትምህርት ከሁሉ በላይ የሆነ ሊከለስ ሊለወጥ የማይችል አማናዊ ቃለ እግዚአብሔር ኦርቶዶክሳዊ
እምነት ይህ ነው፡፡
ይህ ኦርቶዶክሳዊ
እምነት ከራሱ ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ከአለም መካከል እስከ አለም ዳርቻ የተሰበከ በሐዋርያት
አበው በሦስት መቶ አስራ ስምንቱ አበው የጸና ኦርቶዶክሳዊ እምነት ነው፡፡
የአባቶቻችን
ሐይማኖት የቀናች ናት ርትዕት ሃይማኖቶሙ ለቅዱሳን አበዊነ ተብሎ እንደ ተነገረው “ኢታንትጉ ወኢትወሰኩ እምዘ መሐርናክሙ ” እኛ
ካስተማርናችሁ እምነት ሌላ አትጨምሩ አትቀንሱ መልአክ እንኳ ከሰማይ መጥቶ ቢያስተምራችሁ አትቀበሉ ተብሎ ተጽፏል፡፡
ሕገ ሃይማኖት
እንደ ስጋዊ ሥርዓት ተለዋዋጭ አይደለም፡፡ሥጋዊ ሥርዓት ከሰው የተገኘ ስለሆነ እንደ ሰዎች ሥልጣኔ ሊያድግ ይችላል ሕገ ሃይማኖት
ግን የተገኘ ከእግዚአብሔር ስለሆነ የእግዚአብሔር ቃል ከሁሉ በላይ ከማንኛውም የተራቀቀና የመጠቀ ስልጣኔ በላይ ስለሆነ ሕገ እግዚአብሔር
አይለወጥም፡፡ በሕገ ሃይማኖት የጸኑ በትሩፋት የጎለመሱ ኦርቶዶክሳውያን ካህናትና ምእመናን በረድኤተ እግዚአብሔር ተጠብቀው በህጉ
ከብረው በጸጋው ተጎብኝተው ይኖራሉ፡፡
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)
