“ስእለቴን ይዤ ወደ
ቤትህ እገባለሁ” መዝ 65፡13
የእመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያም አባቷ ኢያቄም እናቷ ሐና ይባላሉ፡፡የተወለደችው በእግዚአብሔር ፈቃድ በብስራተ መልአክ ነው፡፡አባትና እናቷ እግዚአብሔርን
ልጅ ብትሰጠን ብለው ተስለው ነበር ሦስት ዓመት ሲሆናት ኢያቄም ለሐና ይህች ልጅ አንድ ነገር ብትሆን ከእግዚአብሔር ከልጃችንም
ሳንሆን እንዳንቀር ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ወስደን እንስጥ ብለው መባ ጨምረው ወደ ቤተመቅደስ ይዘዋት ሄዱ ሊቀ
ካህኑ ዘካርያስ ይባላል ደወል መትቶ ሕዝቡን ሰብስቦ የምግቧ ነገርስ? አለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ
ይዞ ረቦ ታየ፡፡ዘካርያስም ለርሱ የመጣ መስሎት ከእርሱ ሊቀበል ተነሳ ወደ ሰማይም ራቀበት ከእርሱ ቀጥሎ ያለው ሊቀ ካህንም ሊቀበል
ሲቀበርብ ራቀበት፡፡ካህናቱም ሕዝቡም በየተራ ቢቀርቡ ራቀባቸው ምን አልባት ለዚህች ብላቴና የመጣ እንደሆነ እንይ አሉ፡፡ሐናን ትተሻት
እልፍ በይ አሏት፡፡ትታት እልፍ አለች ድክድክ እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን
ጋርዶ በሰው ቁመት ልክ ከመሬት ከፍ አድርጎ መግቧት ዐረገ፡፡ ለቀ ካህኑ ዘካርያስ የምግቧ ነገር ከተያዘ ብሎ ከመካነ ደናግል አስገብቶታል፡፡ኅብስተ
ሰማያዊ ጽዋዐ ሰማያዊ እየተመገበች መላእክት እየጎበኞት አስራ ሁለት አመት በቤተመቅደስ ኖረች፡፡
1. ትምህርት
·
ኢያቄምና
ሐና ጸሎታቸውና ልመናቸው መሰማቱን “እግዚአብሔር የልመናዪን ድምጽ ሰምቶአልና ወደድኩት” (መዝ114፡1)
·
ስለትን
ማክበር
“ተስለህ የማትፈጽም ብትሆን ባትሳል ይሻላል፡፡”
(መክ5፡5)
2. መልእክት
የሰው ልጆችን ልመና የማያስቀር አምላክ የኢያቄምንና የሐናን ጸሎት ሰምቶ የሰጣቸውን አንዲት ልጅ ነቢያት በብዙ ምሳሌ ትንቢት
የተናገሩላትን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በገቡት ቃል ኪዳን መሠረት ለልጃቸው ሳይሳሱ በሦስት ዓመቷ ወደ ቤተመቅደስ ይዘዋት
ሄዱ፡፡እመቤታችን ቀድስት ድንግል ማርያም ሐርና ወርቅ እየፈተለች ሰማያዊ መና እየተመገበች በንጽሕናና በቅድስና ኖረ፡፡በዚህ ዘመን
የምንኖር እኛም እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ ዘወትር ከመቅደሱ ሳንለይና በንጽሕናና በቅድስና እንድንኖር የእናታችን የቅድስት ድንግል
ማርያም አማላጅነትና ጸሎት አይለየን አሜን፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ